Our Notes
👉👉👉ጥብቅ ማሳሰቢያዎች❗️❗️❗️
👉👉👉ጥብቅ ማሳሰቢያዎች❗️❗️❗️
👉ለተማሪዎች
👉ለመምህራን
👉ለተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች/
👉ለት/ት ባለሙያዎች
👉በየደረጃው ላላችሁ አስተዳደር አካላት
👉ለፀጥታ አካላት እና
👉ኃላፊነት ለሚሰማው የትኛውም ዜጋ በሙሉ፡-
ጉዳዩ፡- ለት/ት ጥራት መውደቅ ምክንያት ከሆኑ ችግሮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የተማሪዎች የሰዓት አጠቃቀም በጣም ክፍተት ያለበት መሆኑ ነው፡፡ ችግሩም መቅረፍ የምንችለው በተናጠል ሳይሆን በመነጋገር ተቀናጅተን እና ተናበን መስራት ስንችል ብቻ ነወ፡፡ ለዚህም የያበሩስ ወልቂጤ አጠ/2ኛ ደ/ት/ቤት የሰዓት አጠቃቀም ሪፎርም በቁርጠኝነት ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል፡፡ የት/ቤቱ የቀድሞ ዝናና ክብር እንዲመለስ የሚፈልግ የትኛውም ባለድርሻ አካል ለዚህ ሪፎርም ተባባሪ እንዲሆነን አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ ግልፅ ለማድረግ ያህል፡-
✅ ት/ት ቤት ግቢ የመግቢያ ሰዓት ጠዋት ከ1:30 እስከ 1:50 ብቻ መሆኑን
✅ የሰልፍ ስነ ስረዓት ከ1:50 እስከ 1:53
✅ ወደ ክፍል መግቢያ ከ1:53 እስከ 1:55
✅የስም ጥሪ ማድረጊያ ከ1:55 እስከ 1:58
✅ መ/ራን ለማስተማር ወደ ተመደቡበት ክፍል መግቢያ ከ1:58 እስከ 2:00
✅ መደበኛ መማር ማስተማር የሚጀመረው እና የግቢው መግቢያ በር የሚዘጋው 2:00 አናቱ ላይ መሆኑን ት/ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በመሆኑም፡-
👍የተከበራችሁ ተማሪዎች፡-
✅ ከላይ የተገለፀው ግቢ የመግቢያ ሰዓት በማክበር ኃላፊነታችሁ እንድትወጡ
✅ በተገለፀው ሰዓት መድረስ የማትችሉ መሆኑን ካረጋገጣችሁ /ከረፈደባችሁ/ በመመላለስ ጊዜአችሁን አለማባከን እና ቤት ሆኖ ቤተሰብ በስራ መርዳት፡ ቤት ሆኖ ማንበብ
👍የተከበራችሁ መምህራን
✅ እስካሁን በጀመርነው ልክ አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን
✅ ለዚህ ሪፎርም ውጤታማነት የአንበሳውን ድርሻ በእናንተ እጅ መሆኑን ተረድታችሁ የእስካሁን ቁርጠኝነታችሁ እንዲቀጥል
✅ በ1ኛው ክ/ዜ በስረዓቱ ለተገኙ ተማሪዎች በተለያዩ የመመዘኛ ዘዴዎች መዝኖ ውጤት መስጠት
👍የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች/
✅ ልጆቻችሁ አስቀድመው እንዲደርሱ በጊዜ መሸኘት
✅ ከ2:00 ሰዓት በፊት እንደሚደርሱ እርግጠኛ ካልሆናችሁና እንደሚረፍድባቸው ካረጋገጣችሁ ት/ቤት ብላችሁ እንዳትልኩ
✅ በዚህ መልኩ በሚፈጠር የልጆቻችሁ መንዘላዘልና ባልተገባ ሁኔታ መገኘት ተጠያቂነት መኖሩን እንድትረዱ
👍 የተከበራችሁ የት/ት ባለሙያዎች፣ በየደረጃው ያላችሁ የአስተዳደር አካላት እና የከተማችን ነዋሪዎች
✅ ማህበረሰቡን በማንቃት፤ በት/ት ሰዓት ከት/ቤት ግቢ ወጪ ለሚገኙ ተማሪዎች ምክርና ግንዛቤ በመፍጠር፣
✅ በት/ት ሰዓት ከግቢ ውጪ ባልተገባ ቦታ ለሚገኙ ተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች/ ስለ ልጆቻቸው ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ልጆቸቻውን እንዲከታተሉ መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩን
👍የተከበራችሁ የፀጥታ አካላት
✅ በት/ት ሰዓት ከግቢ ውጪ የሚገኝ ተማሪ ተማሪ ሳይሆን ለሌላ ተልእኮ የተሰማራ ሊሆን ስለሚችል ከት/ቤቱ አካባቢ ማራቅና ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲተባበሩን በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
❤️❤️❤️በመጨረሻም፡-
✅ በተለያዩ አስገዳጅ እና ከባድ ኃላፊነቶች ምክንያት በተገለፀው ሰዓት ግቢ መግባት ለማትችሉ እና ት/ቤቱ ጉዳያችሁ በልዩነት እንዲያይላችሁ የምትፈልጉ ተማሪዎች ከሰኞ ጥቅምት 11/2017 ጀምሮ በማርፈዳችሁ ምክንያት መጉላላት እንዳይፈጠርባችሁ እና ት/ቤቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግላችሁ አሳማኝ መረጃ በመያዝ እሁድ ጥቅምት 10/2017 እሰከ 11:30 ድረስ ባለው ሰዓት ት/ቤት በመቅረብ መረጃ እንድትሰጡ አበክረን እንጠይቃለን፡፡
👍👍❤️መረጃው ለሌሎች በማድረስ ይተባበሩን❗️
"ከሰላምታ ጋር!"
መ/ር ኸይሩ ሞሳ
የት/ቤቱ ተወካይ ር/መ/ር